በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት 12

ወዳጃዊ ስሜትና አሳቢነት ማሳየት

ወዳጃዊ ስሜትና አሳቢነት ማሳየት

1 ተሰሎንቄ 2:7, 8

ፍሬ ሐሳብ፦ አድማጮችህን እንደምትወዳቸውና እንደምታስብላቸው በሚያሳይ መንገድ ተናገር።

ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

  • ስለ አድማጮችህ አስብ። አድማጮችህ ምን ዓይነት ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸው ከግምት ማስገባትህ ከልብ እንድታስብላቸው ያደርግሃል። ካሉባቸው ችግሮች ጋር በተያያዘ ምን እንደሚሰማቸው ለመገመት ሞክር።

  • የምትጠቀምባቸውን ቃላት በጥንቃቄ ምረጥ። አድማጮችህን በሚያጽናና፣ በሚያበረታታ እንዲሁም መንፈሳቸውን በሚያድስ መንገድ ለመናገር ጥረት አድርግ። አድማጮችህን ቅር የሚያሰኝ ነገር ላለመናገር ተጠንቀቅ፤ የይሖዋ ምሥክር ያልሆኑ ሰዎችንም ሆነ የሚያምኑባቸውን ነገሮች ከመንቀፍም መቆጠብ ይኖርብሃል።

  • አሳቢነት አሳያቸው። ደግነት የሚንጸባረቅበት የድምፅ ቃና እንዲሁም ተስማሚ የሆኑ አካላዊ መግለጫዎች ለአድማጮችህ ከልብ እንደምታስብላቸው ያሳያሉ። ፊትህ ላይ የሚንጸባረቀው ስሜት፣ የሚያስተላልፈው መልእክት እንዳለ አስታውስ፤ ፈገግታ አይለይህ።