መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 4 2016 | መጽሐፍ ቅዱስ ምን ፈተናዎችን አልፏል?

ባለፉት ዘመናት፣ መጽሐፍ ቅዱስንና የያዘውን መልእክት ለማጥፋት ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል። የተለያዩ ፈተናዎችን ማለፉ ትኩረት የሚስብ የሆነው ለምንድን ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ልናውቀው የሚገባ ታሪክ

የመጽሐፍ ቅዱስን ያህል የብዙ የሰዎችን እምነት ለረጅም ጊዜ ሲቀርጽ የኖረ መጽሐፍ የለም። ይሁንና በመጽሐፍ ቅዱስ መተማመን እንችላለን?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መጽሐፍ ቅዱስ በስብሶ ከመጥፋት ተርፏል

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችና ገልባጮች መልእክቱን የጻፉት በፓፒረስና በብራና ላይ ነበር። እንዲህ ያሉ ጥንታዊ ቅጂዎች እስከ ዘመናችን ድረስ ሳይበሰብሱ የቆዩት እንዴት ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መጽሐፍ ቅዱስ በተቃዋሚዎች ከመጥፋት ተርፏል

በርካታ የፖለቲካና የሃይማኖት መሪዎች ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ እንዳይኖራቸው፣ እንዳያሳትሙ ወይም እንዳይተረጉሙ ለመከልከል ሞክረዋል። ሆኖም ያደረጉት ሙከራ ሁሉ አልተሳካም።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ተጠብቆ ቆይቷል

አንዳንድ መሰሪ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለመቀየር ጥረት አድርገዋል። ጥረታቸው የከሸፈው እንዴት ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መጽሐፍ ቅዱስ ተጠብቆ የቆየበት ምክንያት

መጽሐፉን ልዩ የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ኢየሱስ የሥጋ ደዌ ሕሙማንን የያዘበት መንገድ አስገራሚ የሆነው ለምንድን ነው? የአይሁድ የሃይማኖት መሪዎች ፍቺን የሚፈቅዱት በምን ምክንያት ነበር?

ከዓመፅ የጸዳ ዓለም ይመጣል?

በዓመፅ ድርጊት ይካፈሉ የነበሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አስተካክለዋል። እነሱን የረዳቸው ነገር ሌሎችንም ሊጠቅም ይችላል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል

ብዙ ጊዜ ብሸነፍም በመጨረሻ ተሳካልኝ

ይህ ሰው የፖርኖግራፊ ሱሱን አሸንፎ አምላክ የሚሰጠውን የአእምሮ ሰላም ሊያገኝ የቻለው እንዴት ነው?

ልታደርገው የሚገባ ጠቃሚ ንጽጽር

ሺህ የሚቆጠሩ የክርስትና ሃይማኖቶች እርስ በርሱ በሚጋጭ መሠረተ ትምህርትና አመለካከት ተከፋፍለዋል። እውነቱን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

አምላክ ሰዎች ወደ እሱ እንዲቀርቡ ለማድረግ አንድ የሃይማኖት ድርጅት ይጠቀማል?

በተጨማሪም . . .

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ሐሳብ የያዘ መጽሐፍ ነው?

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አምላክ መርቷቸው እንደጻፉ ተናግረዋል። እንዲህ ያሉት ለምንድን ነው?