በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የቱካን ምንቃር

የቱካን ምንቃር

ንድፍ አውጪ አለው?

የቱካን ምንቃር

በማዕከላዊና በደቡብ አሜሪካ የሚገኘው ቱካን የተባለ የወፍ ዝርያ የመብረር ችሎታው በጣም ደካማ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ከቦታ ወደ ቦታ የሚዘዋወረው እየዘለለ ነው። አንዳንድ የቱካን ዝርያዎች የሚያሰሙት ድምፅ ከእንቁራሪት ድምፅ ጋር የሚመሳሰል ሲሆን ኃይለኛ በመሆኑ በደን ውስጥ እስከ አንድ ኪሎ ሜትር ድረስ ይሰማል። ሳይንቲስቶችን ይበልጥ የሚያስደንቀው ግን የቱካን ምንቃር ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ የአንዳንድ ቱካኖች ምንቃር ርዝመት ከወፉ ቁመት አንድ ሦስተኛ በላይ ይሆናል። ምንቃሩ እንዲሁ ሲታይ ክብደት ያለው ይምሰል እንጂ ከባድ አይደለም። የቁስ አካል ሳይንስ ምሁር የሆኑት ማርክ አንድሬ ማየርስ እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል፦ “የምንቃሩ የውጪኛው ክፍል የተሠራው ጥፍራችንና ፀጉራችን ከተሠራበት ኬራቲን ከተባለ ንጥረ ነገር ነው። . . . ከዚህም በላይ እንደ ጣሪያ ክዳን እርስ በርስ የተደራረቡ ጥቃቅን ባለ ስድስት ጎን ንጣፎች ንብርብር ነው።”

የቱካን ምንቃር ይዘት ጠንካራ ከሆነ ስፖንጅ ጋር ይመሳሰላል። አንዳንድ ቦታዎች ላይ ክፍተት ያለው ሲሆን ሌሎች ክፍሎቹ ደግሞ እንደ ርብራብና እንደ ገለፈት ባሉ ነገሮች የተሠሩ ናቸው። ይህም ክብደቱ ቀላል እንዲሆንና አስደናቂ የሆነ ጥንካሬ እንዲኖረው አስተዋጽኦ አድርጓል። ማየርስ፣ ቱካን በረቀቀ መንገድ የተሠራ ምንቃር ያለው መሆኑ “በጣም የጠለቀ የመካኒካል ኢንጂነሪንግ እውቀት ያለው አስመስሎታል” ብለዋል።

የቱካን ምንቃር የተሠራበት መንገድ ኃይለኛ ግጭትን እንኳ ሳይቀር እንዲቋቋም ያስችለዋል። የዚህ ወፍ ምንቃር በአውሮፕላንና በመኪና ኢንዱስትሪ ለተሰማሩ መሐንዲሶች በሞዴልነት ሊያገለግል እንደሚችል ሳይንቲስቶች ያምናሉ። ማየርስ “ከቱካን ምንቃር ጋር ተመሳሳይነት ባለው መንገድ የተሠራ የመኪናዎች አካል በአደጋ ጊዜ አሽከርካሪዎች ከባድ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሊከላከል ይችላል” በማለት ተናግረዋል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ቀላልና በጣም ጠንካራ የሆነው የቱካን ምንቃር እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 17 ላይ የሚገኝ ሥዕላዊ መግለጫ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

መሃል ላይ ያለ ክፍተት

እንደ ስፖንጅ ያለ ነገር