በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 ንድፍ አውጪ አለው?

የባር ቴይልድ ጎድዊት አቅጣጫ የማወቅ ችሎታ

የባር ቴይልድ ጎድዊት አቅጣጫ የማወቅ ችሎታ

ባር ቴይልድ ጎድዊት የተባለው ወፍ ከቦታ ወደ ቦታ የሚፈልስበት መንገድ በጣም አስደናቂ ነው። ይህ ወፍ በሚፈልስበት ጊዜ 11,000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ጉዞ ለማድረግ ከስምንት ቀናት በላይ ይፈጅበታል።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ አንዳንድ አእዋፍ በአንጎላቸው ውስጥ የተገጠመ ኮምፓስ ያላቸው ያህል አቅጣጫን የሚያውቁት በምድር መግነጢሳዊ መስክ (ማግኔቲክ ፊልድ) አማካኝነት እንደሆነ ተመራማሪዎች ይገምታሉ። በተጨማሪም ጎድዊት የተባለው ወፍ አቅጣጫውን የሚያውቀው ቀን ላይ በፀሐይ፣ ሌሊት ላይ ደግሞ በከዋክብት አማካኝነት ሊሆን ይችላል። ከዚህም በላይ ይህ ወፍ ከኋላው ሊገፋው የሚችል ነፋስ እየመጣ እንደሆነ የማወቅ ችሎታ ሳይኖረው አይቀርም። ያም ሆኖ እነዚህ ወፎች ይህን ለማመን የሚያዳግት ረጅም ጉዞ የሚያደርጉት እንዴት እንደሆነ በዝርዝር ማወቅ ለሊቃውንቱ አዳጋች ሆኖባቸዋል። የሥነ ሕይወት ተመራማሪ የሆኑት ቦብ ጊል “እነዚህን ወፎች ላለፉት 20 ዓመታት ሳጠናቸው ብቆይም ሁልጊዜ ያስደምሙኛል” ብለዋል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ጎድዊት የተባለው ወፍ አቅጣጫ የማወቅ ችሎታ በዝግመተ ለውጥ የመጣ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?