በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘እንደ እነዚህ ያሉትን ሰዎች በአክብሮት ያዟቸው’

‘እንደ እነዚህ ያሉትን ሰዎች በአክብሮት ያዟቸው’

ከ1992 ጀምሮ የበላይ አካሉ በሥሩ ያሉት ኮሚቴዎች ለሚያከናውኑት ሥራ ድጋፍ የሚሰጡ ተሞክሮ ያካበቱና የጎለመሱ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ሲሾም ቆይቷል። * “የሌሎች በጎች” አባላት የሆኑት እነዚህ ረዳቶች ለበላይ አካሉ ከፍተኛ እገዛ ያበረክታሉ። (ዮሐ. 10:16) እነዚህ ወንድሞች የተመደቡበት ኮሚቴ በሚያደርገው ሳምንታዊ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከአንድ ጉዳይ ጋር ተያያዥነት ያለው መረጃ ይሰጣሉ፤ እንዲሁም ጠቃሚ ሐሳብ ያቀርባሉ። የመጨረሻውን ውሳኔ የሚያደርጉት የበላይ አካሉ አባላት ናቸው። ይሁንና ረዳቶቹ ኮሚቴው የሚሰጣቸውን መመሪያ ተግባራዊ ያደርጋሉ፤ እንዲሁም የተሰጣቸውን ማንኛውንም ሥራ ያከናውናሉ። ረዳት ሆነው የሚያገለግሉት ወንድሞች የበላይ አካል አባላት ለልዩና ለብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ወደተለያዩ ቦታዎች ሲጓዙ አብረዋቸው ይሄዳሉ። ከዚህ በተጨማሪ የዋናው መሥሪያ ቤት ተወካዮች በመሆን ቅርንጫፍ ቢሮዎችን እንዲጎበኙ ሊመደቡ ይችላሉ።

ይህ ዝግጅት ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ሲያገለግል የቆየ አንድ ረዳት “እኔ የተሰጠኝን ሥራ በሚገባ ስወጣ የበላይ አካሉ ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ይበልጥ ትኩረት መስጠት ይችላል” ብሏል። አንድ ሌላ ወንድም ደግሞ ረዳት ሆኖ ያገለገለባቸውን ከ20 የሚበልጡ ዓመታት በተመለከተ “ይህ አገልግሎት ላስበው ከምችለው በላይ ትልቅ መብት ነው” ሲል ገልጿል።

የበላይ አካሉ ለረዳቶቹ ከፍተኛ ኃላፊነት የሰጠ ከመሆኑም ሌላ እነዚህ ታማኝና ታታሪ ወንድሞች የሚያከናውኑትን ጠቃሚ አገልግሎት በአድናቆት ይመለከታል። ሁላችንም ‘እንደ እነዚህ ያሉትን ሰዎች በአክብሮት እንያዛቸው።’—ፊልጵ. 2:29

^ አን.2 የበላይ አካሉ ስድስት ኮሚቴዎች የተጣሉባቸውን ኃላፊነቶች በተመለከተ አጠር ያለ ማብራሪያ ለማግኘት የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው! በተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 12 ላይ የሚገኘውን “የበላይ አካሉ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የሚያከናውነው እንዴት ነው?“ የሚለውን ሣጥን ተመልከት።