በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 50

ራሴን ለአምላክ ለመወሰን ያቀረብኩት ጸሎት

ራሴን ለአምላክ ለመወሰን ያቀረብኩት ጸሎት

(ማቴዎስ 22:37)

  1. 1. ጥበብን ይውደድ ልቤ፤

    ያስደስትህ ሐሳቤ።

    ላንተ ክብር፣ ውዳሴ

    ልዘምር ባንደበቴ።

  2. 2. ከት’ዛዝህ አልወጣም፤

    ሕጎችህን አልረሳም።

    አልሳሳም ለንብረቴ፤

    ያንተ ነው ውድ አባቴ።

  3. 3. ሕይወቴም የአንተው ነው፤

    ፈቃድህን እሻለሁ።

    ምንም ሳልቆጥብ ራሴን፣

    እሰጥሃለሁ ነፍሴን።

(በተጨማሪም መዝ. 40:8⁠ን፣ ዮሐ. 8:29⁠ን እና 2 ቆሮ. 10:5⁠ን ተመልከት።)