በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 7

ይሖዋ ኃይላችን

ይሖዋ ኃይላችን

(ኢሳይያስ 12:2)

  1. 1. ታላቅ ይሖዋ ብርታት፣ ኃይላችን፤

    ባንተ ደስ ይለናል አዳኛችን።

    ሰዎች ቢሰሙንም ባይሰሙንም፣

    መመሥከራችንን አናቆምም።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ’ምባችን፣ ብርታት፣ ኃይላችን፤

    ስምህን ’ናስታውቅ ሌትና ቀን።

    ሁሉን ቻይ ይሖዋ ተገናችን፣

    መሸሸጊያችን ነህ፤ መከታችን።

  2. 2. ደስ ብሎናል፣ እውነትን አወቅን፤

    ብርሃን አየን፣ ማስተዋል አገኘን።

    ት’ዛዝህን ከቃልህ አውቀናል፤

    ለመንግሥትህ ለመቆም መርጠናል።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ’ምባችን፣ ብርታት፣ ኃይላችን፤

    ስምህን ’ናስታውቅ ሌትና ቀን።

    ሁሉን ቻይ ይሖዋ ተገናችን፣

    መሸሸጊያችን ነህ፤ መከታችን።

  3. 3. እንታዘዝሃለን በደስታ፤

    አንተ ብቻ ነህ የኛ አለኝታ።

    ሊያጠቃን ቢነሳብንም ሰይጣን፣

    እስከ ሞት ታማኝ እንድንሆን እርዳን።

    (አዝማች)

    ይሖዋ ’ምባችን፣ ብርታት፣ ኃይላችን፤

    ስምህን ’ናስታውቅ ሌትና ቀን።

    ሁሉን ቻይ ይሖዋ ተገናችን፣

    መሸሸጊያችን ነህ፤ መከታችን።

(በተጨማሪም 2 ሳሙ. 22:3⁠ን፣ መዝ. 18:2⁠ን እና ኢሳ. 43:12⁠ን ተመልከት።)