በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 73

ድፍረት ስጠን

ድፍረት ስጠን

(የሐዋርያት ሥራ 4:29)

  1. 1. ስንሰብክ ስለ መንግሥትህ፣

    ስናውጅ ስለ ስምህ፣

    ብዙዎች ይቃወሙናል፤

    ደግሞም ያንቋሽሹናል።

    አይበጅም ሰውን መፍራት፤

    አንተን መታዘዝ ይገባል።

    ስለዚህ ይድረስ ጸሎታችን፤

    ስጠን ’ባክህ መንፈስህን።

    (አዝማች)

    ለመመሥከር ድፍረት ስጠን፤

    ልበ ሙሉ አድርገን።

    ፍርሃታችንን አጥፋልን፤

    ዓለም እንዲያውቅህ አንተን።

    በጣም ቀርቧል አርማጌዶን፤

    እስከዚያው ግን ድፍረት ስጠን።

    አምላክ ሆይ ልመናችንን፣

    ’ባክህ ስማን።

  2. 2. ፍርሃት ቢያድርም በውስጣችን፣

    ታውቃለህ ደካሞች ነን።

    ቃል ገብተሃል ልትደግፈን፤

    በዚህም እምነት አለን።

    ይሖዋ ሆይ ተመልከት፤

    ሲደርስብን ዛቻ፣ ስደት።

    መመሥከር እንድንችል በጽናት፣

    እርዳን የሰማዩ አባት።

    (አዝማች)

    ለመመሥከር ድፍረት ስጠን፤

    ልበ ሙሉ አድርገን።

    ፍርሃታችንን አጥፋልን፤

    ዓለም እንዲያውቅህ አንተን።

    በጣም ቀርቧል አርማጌዶን፤

    እስከዚያው ግን ድፍረት ስጠን።

    አምላክ ሆይ ልመናችንን፣

    ’ባክህ ስማን።

(በተጨማሪም 1 ተሰ. 2:2⁠ን እና ዕብ. 10:35⁠ን ተመልከት።)