በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ነቅታችሁ ጠብቁ!

የይሖዋ ምሥክሮችና የሆሎኮስት ጥቃት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የይሖዋ ምሥክሮችና የሆሎኮስት ጥቃት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ጥር 27, 2023 የሆሎኮስት መታሰቢያ በዓለም ዙሪያ የሚታሰብበት ቀን ነው። አንዳንዶች ከዛሬ 75 ዓመት በፊት የተፈጸመውን ይህን አሰቃቂ ጥቃት ሲያስቡ አምላክ ያላስቆመው ለምንድን ነው ብለው ይጠይቃሉ።

 የአሰቃቂው የሆሎኮስት ጥቃት ገፈት ቀማሾች የአይሁድ ሕዝብ ናቸው። በተቀናጀው የግድያ ዘመቻ ሚሊዮኖች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሆሎኮስት ወቅት የጥቃት ዒላማ የሆኑና ጭፍጨፋ የደረሰባቸው ሌሎች ቡድኖችም አሉ። ለምሳሌ፣ የይሖዋ ምሥክሮች የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርቶች ስለሚከተሉ ስደት ደርሶባቸዋል።

‘የተሻለ ሕይወትና ተስፋ’

 ብዙዎች፣ እንደ ሆሎኮስት ያለ ጥቃት ዳግም እንዳይከሰት ይሰጋሉ። ደስ የሚለው ግን እንዲህ ያሉ ሰቆቃዎች የማይኖሩበት ጊዜ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።

  •   “‘ለእናንተ የማስበውን ሐሳብ በሚገባ አውቀዋለሁና’ ይላል ይሖዋ፤ ‘ለእናንተ የማስበው ጥፋትን ሳይሆን ሰላምን እንዲሁም የተሻለ ሕይወትንና ተስፋን ነው።’”—ኤርምያስ 29:11 a

 ይሖዋ አምላክ በቅርቡ እርምጃ ሲወስድ ይህ ተስፋ እውን ይሆናል፤ አምላክ ክፋትን ያስወግዳል እንዲሁም ክፋት ያስከተላቸውን ጉዳቶች ይሽራል። በቅርቡ፣

  •   በሌሎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ክፉዎችን ያጠፋል።—ምሳሌ 2:22

  •   ግፍ የደረሰባቸውን ሰዎች ቁስል ያክማል።—ራእይ 21:4

  •   የሞቱትን አስነስቶ በምድር ላይ ሕይወት ይሰጣቸዋል።—ዮሐንስ 5:28, 29

 መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን አጽናኝ ተስፋ ልትተማመንበት ትችላለህ። ለምን የሚለውን ማወቅ ትፈልጋለህ? በአስተማሪ እገዛ በነፃ የምንሰጠውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለምን አትሞክረውም?

a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18