በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ምድር እየጠፋች ነው—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ምድር እየጠፋች ነው—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው መዘዝ ወደ ጥፋት እያንደረደረን ነው። ትላልቅ ከተሞች በውኃ ሊዋጡ ነው። ሆኖ የማያውቅ የሙቀት ወጀብ እየታየ ነው። አውዳሚ አውሎ ነፋሶች እየተከሰቱ ነው። በብዙ ቦታዎች የውኃ እጥረት ተከስቷል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዕፀዋትና እንስሳት ከምድር ገጽ እየጠፉ ነው። ይህ ምናብ የፈጠረው ወይም የተጋነነ ወሬ አይደለም። ሳይንስ በግልጽ የሚናገረው ሐቅ ነው። የኃይል አጠቃቀም ፖሊሲያችንን ካልቀየርን ይህ መከሰቱ አይቀርም።”—የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሆኑት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የአየር ንብረትን ለውጥ የሚመለከተው የመንግሥታቱ ፓነል ሚያዝያ 4, 2022 ያወጣውን ሪፖርት አስመልክተው የተናገሩት።

“ሳይንቲስቶች [በዩናይትድ ስቴትስ] የሚገኙት 423 ብሔራዊ ፓርኮች በሙሉ ማለት ይቻላል በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ጉዳት እንደሚደርስባቸው እያስጠነቀቁ ነው፤ ይህ የሚሆነው የሙቀቱ መጠን መጨመር በእነዚህ ፓርኮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስለሚያደርስ ነው። ሰደድ እሳትና የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የበረዶ ግግር መቅለጥ፣ የባሕር ጠለል ከፍታ መጨመር፣ የሙቀት ወጀብ፤ የሰው ልጅ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተገለጹት መቅሰፍቶች ጋር የሚመሳሰሉ አደገኛ ሁኔታዎች ተጋርጠውበታል።”—“በየሎውስቶን ጎርፍ ያስከተለው ጉዳት፣ የሚጠብቀንን ቀውስ አመላካች ነው”—ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ሰኔ 15, 2022

ምድራችን የተጋረጡባት የአየር ንብረት ችግሮች መፍትሔ አላቸው? ከሆነስ ይህን ችግር የሚፈታው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እስቲ እንመልከት።

በምድራችን ላይ ጉዳት እንደሚደርስ ትንቢት ተነግሯል

መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ “ምድርን እያጠፉ ያሉትን [እንደሚያጠፋ]” ተናግሯል። (ራእይ 11:18) ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሦስት ነገሮችን እንረዳለን፦

  1. 1. የሰው ልጅ የሚያደርገው ነገር ምድር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።

  2. 2. ምድር ላይ የሚደርሰው ጉዳት የሚያበቃበት ጊዜ ይመጣል።

  3. 3. ምድራችን ያጋጠማትን ቀውስ የሚያስተካክሉት የሰው ልጆች ሳይሆኑ አምላክ ነው።

የምድራችን ዕጣ ፋንታ አስተማማኝ ነው

መጽሐፍ ቅዱስ “ምድር . . . ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች” ይላል። (መክብብ 1:4) ስለዚህ ምንጊዜም ቢሆን የሰው ልጆች ይኖሩባታል።

  • “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።”—መዝሙር 37:29

ምድራችን ሙሉ በሙሉ ትታደሳለች።

  • “ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ሐሴት ያደርጋል፤ በረሃማው ቦታም ደስ ይለዋል፤ እንደ ሳሮን አበባም ያብባል።”—ኢሳይያስ 35:1