በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 20, 2019
ሜክሲኮ

ሞንተሬ፣ ሜክሲኮ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ሞንተሬ፣ ሜክሲኮ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከሰኔ 7-9, 2019

  • ቦታ፦ ቢቢቪኤ ባንኮሜር ስታዲየም፣ ሞንተሬ፣ ሜክሲኮ

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ስፓንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ የሜክሲኮ ምልክት ቋንቋ

  • ፕሮግራሙ የተላለፈባቸው ቦታዎች፦ በ6 አገሮች (ሆንዱራስ፣ ሜክሲኮ፣ ኒካራጓ፣ ኮስታ ሪካ፣ ጓቴማላ እና ፓናማ) ውስጥ ባሉ 38 ቦታዎች

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 39,099

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 393

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 4,682

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ስፔን፣ ብራዚል፣ ኔዘርላንድስ፣ አርጀንቲና፣ ኮሎምቢያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ፓራጓይ፣ ፔሩ

  • ተሞክሮ፦ የጓዴሎፕ ከተማ ከንቲባ ተወካይ የሆኑት ሮቤርቶ ቫሌሮ ቅዳሜ ዕለት ስብሰባውን ጎብኝተው ነበር። እንዲህ የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፦ “የመንግሥታችን ዋነኛ ግብ የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ ነው። እናንተ የይሖዋ ምሥክሮች ደግሞ መልካም ዜጎች በመሆን ለዚህ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታችኋል። የከተማው ሕዝብ በሙሉ ይህን ያውቃል።”

 

ወንድሞችና እህቶች በሞንተሬ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ልዑካኑን ሲቀበሉ

ልዑካኑ ወደ ስብሰባ ቦታው ሲደርሱ፤ ውብ የሆነው ሲላ ተራራ ከሩቅ ይታያል

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ማርክ ሳንደርሰን የዓርብን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ

ቅዳሜ ዕለት አንድ ሰው ከአራቱ የጥምቀት ገንዳዎች በአንዱ ውስጥ ሲጠመቅ

ከዓለም ዙሪያ የመጡት ልዑካን ስብሰባውን በጥሞና ሲያዳምጡ

ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በስብሰባው የመጨረሻ ቀን ላይ ሕዝቡን ሲሰናበቱ

ከአፖዳካ የመጣ አንድ ቤተሰብ አባላት ‘እንወዳችኋለን’ የሚል ጽሑፍ ይዘው

አንዲት ልዑክ በአካባቢው ከምትኖር እህት ጋር ሆና ስትሰብክ

ልዑካኑ በሰሜናዊ ሚክሲኮ የተለመደውን ፖልካ ኖርቴና የተባለ ውዝዋዜ ሲመለከቱ

እህቶች ሜክሲኮ ውስጥ የሚገኘውን የጃሊሶ ግዛት ባሕላዊ ውዝዋዜ ሲያሳዩ