በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በፔትሪንያ፣ ክሮኤሺያ በሚገኝ አውራ ጎዳና ላይ የሚገኙ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሕንፃዎች

ጥር 8, 2021
ክሮኤሺያ

ክሮኤሺያ በከባድ የምድር መናወጥ ተመታች

ክሮኤሺያ በከባድ የምድር መናወጥ ተመታች

ቦታ

ከዛግሬብ፣ ክሮኤሺያ በስተ ደቡብ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ፔትሪንያ ከተማ አቅራቢያ

የደረሰው አደጋ

  • ታኅሣሥ 29, 2020 ክሮኤሺያ በምድር መናወጥ መለኪያ 6.4 በተመዘገበ የምድር መናወጥ ተመታች። በክሮኤሺያ ታሪክ እንዲህ ያለ ከባድ የምድር መናወጥ ተመዝግቦ አያውቅም

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • በአካባቢው ከሚኖሩት 91 አስፋፊዎች መካከል አንዳቸውም አካላዊ ጉዳት አልደረሰባቸውም

  • 29 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 9 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 16 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • በሲሳክ የሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የክሮኤሺያ ቅርንጫፍ ቢሮ፣ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሟል። ኮሚቴው ከሁለት የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ከአካባቢው የጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር መንፈሳዊ ማበረታቻ እና የእርዳታ ቁሳቁስ እያቀረበ ነው፤ በአደጋው ምክንያት ከቤታቸው የተፈናቀሉ አስፋፊዎችም ጊዜያዊ ማረፊያ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ነው። የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ይሖዋ ለወንድሞቻችን በዚህ አስጨናቂ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን ብርታት እንዲሰጣቸው እንጸልያለን።—1 ጴጥሮስ 5:10