በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 20, 2022
ዓለም አቀፋዊ ዜና

በJW Library አማካኝነት ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ጽሑፍ በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት

በJW Library አማካኝነት ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ጽሑፍ በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት

ጥር 2021 የበላይ አካሉ ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለው መጽሐፍና ብሮሹር መውጣታቸውን አበሰረ። እነዚህ ጽሑፎችና እነሱን ለማስጠናት የምንጠቀምበት አሳታፊ የማስተማሪያ ዘዴ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን በመምራት ረገድ ይበልጥ ውጤታማ እንድንሆን ረድቶናል።

በዲጂታል ፎርማት የተዘጋጀው መጽሐፍና ብሮሹር ለአስጠኚዎችም ሆነ ለጥናቶች ይበልጥ ማራኪና አሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ JW Library አፕሊኬሽን ላይ አዳዲስ ገጽታዎች ተጨምረዋል። ጊዜ ወስደህ ከእነዚህ አዳዲስ ገጽታዎች ጋር ለመተዋወቅ ጥረት እንድታደርግ እናበረታታሃለን።

  • ጥናትህ በምዕራፉ ውስጥ ያለን አንድ ነጥብ እንዲያገኝ ትፈልጋለህ? አንቀጹን ስትጫን መምረጫ ይመጣልሃል። አጋራ የሚለውን ስትመርጥ ወደምትፈልገው አንቀጽ የሚወስድ ሊንክ መላክ ትችላለህ።

  • የአንድን አንቀጽ የድምፅ ቅጂ ከጥናትህ ጋር መስማት ትፈልጋለህ? አንቀጹን ስትጫን መምረጫ ይመጣልሃል። አጫውት የሚለውን ስትመርጥ የድምፅ ቅጂውን ከዚያ አንቀጽ ጀምሮ ማጫወት ትችላለህ።

  • አንተ የምትጠቀመው ዲጂታል ፎርማት ቢሆንም ጥናትህ የሚጠቀመው የታተመውን ጽሑፍ ነው እንበል። የታተመው ገጽ ምን እንደሚመስል ማየት ትፈልጋለህ? ተጨማሪ አማራጮች (ከላይ በስተ ቀኝ ያሉት ሦስት ነጠብጣቦች) ከሚለው ላይ ለሕትመት የተቀናበረ የሚለውን ምረጥ። ወደ ዲጂታል ፎርማት ለመመለስ ደግሞ እዚያው ቦታ ሄደህ ለዲጂታል የተዘጋጀ የሚለውን ምረጥ።

  • ጥናቶችህ በዲጂታል ፎርማት በተዘጋጀው ጽሑፍ ላይ እድገታቸውን እንዲመዘግቡ ትፈልጋለህ? አንድን ምዕራፍ ያጠናቀቁበትን ቀን ለመመዝገብ ወይም ያወጡትን ግብ ለመጻፍ ለዚያ ዓላማ የተዘጋጁትን ሣጥኖች እንዲጠቀሙ አበረታታቸው። “የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን መዝግብ” በሚለው ክፍል ላይ ያሉትን ምልክት ማድረጊያዎችም መጠቀም ይችላሉ።