በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በጉዋም በሚገኝ ዴዴዶ የተባለ መንደር የሚኖሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የተጎዱ ቤቶች

ሰኔ 19, 2023
ጉዋም

ማዋር የተባለ አውሎ ነፋስ ጉዋምን እና ሮታን መታ

ማዋር የተባለ አውሎ ነፋስ ጉዋምን እና ሮታን መታ

ግንቦት 24, 2023 ማዋር የተባለው አውሎ ነፋስ የጉዋም እና የሮታ ደሴቶችን መታ። ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በአካባቢው እንዲህ ያለ ከባድ አውሎ ነፋስ ተከስቶ አያውቅም። በእነዚህ ደሴቶች ላይ ከ70 ሴንቲ ሜትር የሚበልጥ ዝናብ የጣለ ሲሆን አውሎ ነፋሱም በሰዓት 160 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ነበረው። አውዳሚ በነበረው ነፋስና ከባድ ዝናብ ምክንያት በአብዛኞቹ የጉዋምና የሮታ ክፍሎች ውኃና ኤሌክትሪክ ተቋርጧል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል የተጎዳ ወይም የሞተ የለም

  • 3 ቤቶች ወድመዋል

  • 12 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 8 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች በአውሎ ነፋሱ ለተጎዱት ማበረታቻ እየሰጡና ተግባራዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው

  • የእርዳታ ሥራውን ለማደራጀት 2 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

የተፈጥሮ አደጋዎችን የማንፈራበትንና ሁላችንም ‘በብዙ ሰላም እጅግ የምንደሰትበትን’ ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።—መዝሙር 37:11