በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ስንሞት ምን እንሆናለን?

ስንሞት ምን እንሆናለን?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መጽሐፍ ቅዱስ “ሕያዋን እንደሚሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን ምንም አያውቁም” ይላል። (መክብብ 9:5፤ መዝሙር 146:4) በመሆኑም ስንሞት ሕልውናችን ያከትማል ማለት ነው። የሞቱ ሰዎች ማሰብም ሆነ መሥራት አይችሉም፤ እንዲሁም ምንም ዓይነት ስሜት የላቸውም።

“ወደ ዐፈር ትመለሳለህ”

 አምላክ፣ ስንሞት ምን እንደምንሆን ለመጀመሪያው ሰው ማለትም ለአዳም ነግሮታል። አዳም ታዛዥ ባለመሆኑ አምላክ “ዐፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ” ብሎታል። (ዘፍጥረት 3:19) አምላክ አዳምን “ከምድር ዐፈር” ከመፍጠሩ በፊት አዳም ሕልውና አልነበረውም። (ዘፍጥረት 2:7) ስለሆነም አዳም ሲሞት ወደ አፈር ተመለሰ፤ በሌላ አባባል ሕልውናው አከተመ።

 በዛሬው ጊዜም አንድ ሰው ሲሞት የሚያጋጥመው ነገር ተመሳሳይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎችንም ሆነ እንስሳትን አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉም ከዐፈር እንደ ሆኑ፣ ተመልሰው ወደ ዐፈር ይሄዳሉ።”​—መክብብ 3:19, 20

ሞት የሁሉ ነገር መጨረሻ ነው?

 መጽሐፍ ቅዱስ ሞትን ብዙውን ጊዜ ከእንቅልፍ ጋር ያመሳስለዋል። (መዝሙር 13:3፤ ዮሐንስ 11:11-14፤ የሐዋርያት ሥራ 7:60) ከባድ እንቅልፍ ውስጥ ያለ ሰው በአካባቢው ስለሚከናወነው ነገር ምንም አያውቅም። በተመሳሳይም የሞቱ ሰዎች ምንም ነገር አያውቁም። ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ የሞቱ ሰዎችን ከእንቅልፋቸው የማንቃት ያህል እንደሚቀሰቅሳቸውና መልሶ ሕይወት እንደሚሰጣቸው ይናገራል። (ኢዮብ 14:13-15) አምላክ ከሞት ለሚያስነሳቸው ሰዎች ሞት የሁሉ ነገር መጨረሻ አይደለም