በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች፣ እውነተኛው ሃይማኖት የእነሱ ብቻ እንደሆነ ይሰማቸዋል?

የይሖዋ ምሥክሮች፣ እውነተኛው ሃይማኖት የእነሱ ብቻ እንደሆነ ይሰማቸዋል?

 ሃይማኖትን በቁም ነገር የሚይዙ ሰዎች የሚመርጡት እምነት በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው። አለበለዚያ ሃይማኖት መያዛቸው ምን ጥቅም አለው?

 ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ወደ መዳን የሚያደርሱ የተለያዩ ሃይማኖቶች ወይም መንገዶች እንዳሉ አላስተማረም። ከዚህ ይልቅ እንዲህ ብሏል፦ “ወደ ሕይወት የሚያስገባው በር ግን ጠባብ መንገዱም ቀጭን ነው፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።” (ማቴዎስ 7:14) የይሖዋ ምሥክሮች ይህን መንገድ እንዳገኙት ያምናሉ። ይህ ባይሆን ኖሮ ሌላ ሃይማኖት ይፈልጉ ነበር።