በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ማንበብና መጻፍ ተማሩ

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ማንበብና መጻፍ ተማሩ

በ2011 የይሖዋ ምሥክሮች ከ5,700 የሚበልጡ ሰዎች ማንበብና መጻፍ እንዲችሉ ረድተዋል።

ጋና፦

ባለፉት 25 ዓመታት ከ9,000 የሚበልጡ ሰዎችን ማንበብና መጻፍ አስተምረናል።

ዛምቢያ፦

ከ2002 ወዲህ 12,000 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች የማንበብና የመጻፍ ችሎታቸውን አሻሽለዋል። የ82 ዓመት አረጋዊት የሆኑት አግነስ እንዲህ ብለዋል፦ “በጉባኤ ውስጥ የማንበብና መጻፍ ትምህርት መሰጠት እንደሚጀምር ማስታወቂያ ሲነበብ በደስታ ተመዘገብኩ። በመጀመሪያው የትምህርት ቀን ስሜን መጻፍ ቻልኩ!”

ፔሩ፦

አንዲት የ55 ዓመት ተማሪ እንዲህ ስትል ጽፋለች፦ “ወላጆቼ ትምህርት ቤት አላስገቡኝም፤ ስለዚህ ማንበብና መጻፍ እችላለሁ ብዬ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም።”

ሞዛምቢክ፦

ባለፉት 15 ዓመታት ከ19,000 የሚበልጡ ሰዎች ማንበብ ተምረዋል። ፌሊዛርዳ የተባለች አንዲት ተማሪ እንዲህ ብላለች፦ “የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን መፈለግና ለሌሎች ማንበብ ስለቻልኩ ተደስቻለሁ። ከዚህ በፊት እንዲህ ማድረግ በጣም ይከብደኝ ነበር።”

የሰለሞን ደሴቶች፦

በሰለሞን ደሴቶች የሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “ቀደም ባሉት ዓመታት፣ ራቅ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ትምህርት ቤት የመግባት አጋጣሚ አልነበራቸውም። በተጨማሪም መደበኛ ትምህርት ያገኙት ሴት ልጆች ቁጥር በጣም አነስተኛ ነበር። በመሆኑም በርካታ አዋቂ ሰዎች ከተዘጋጀው የማንበብና መጻፍ ትምህርት ተጠቅመዋል። ብዙዎቹ ትምህርቱን ካጠናቀቁ በኋላ በራስ የመተማመን ስሜታቸው ጨምሯል።”