መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 3 2019 | ሕይወት በቃ ይኸው ነው?

ጥያቄው ሁላችንንም ይመለከታል፤ መልሱን ማወቃችን በሕይወታችን ላይ ለውጥ ያመጣል።

ከሞት የሚያመልጥ የለም

ምንም ያህል ጥረት ብናደርግ ከእርጅናና ከሞት ማምለጥ አንችልም። ሕይወት በቃ ይኸው ነው?

ረጅም ዕድሜ ለመኖር የሚደረግ ጥረት

አንዳንድ የባዮሎጂና የጄኔቲክስ ተመራማሪዎች የእርጅናን መንስኤ ለማወቅ እየሞከሩ ነው። ጥረታቸው ምን ውጤት አስገኘ?

የተፈጠርነው ለዘላለም እንድንኖር ነው

ደስተኛ ሆኖ ለረጅም ዘመን መኖር የማይፈልግ ማን አለ?

የምናረጀውና የምንሞተው ለምንድን ነው?

የአምላክ ዓላማ ሰዎች እንዲሞቱ አልነበረም። አዳምና ሔዋን ፍጹም አካልና ፍጹም አእምሮ ነበራቸው፤ አሁንም ድረስ መኖር ይችሉ ነበር።

ጠላታችን ሞት የሚጠፋው እንዴት ነው?

አምላክ ቤዛውን በመክፈል የሰው ዘር ከሞት ነፃ የሚወጣበትን ዝግጅት አደረገ።

የዘላለም ሕይወት ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

አምላክ ለሚወዳቸው ሰዎች ያዘጋጀውን ሕይወት ማግኘት ከፈለግክ በሕይወት ‘መንገድ’ ላይ መጓዝ ይኖርብሃል።

በአሁኑ ጊዜም አስደሳች ሕይወት መምራት ይቻላል

የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር ባለህ ነገር ለመርካት፣ የጤና ችግሮችን ለመቋቋምና ትዳርህን ለማጠናከር የሚረዳህ እንዴት ነው?

የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ መልሱን ይሰጠናል።