በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጤንነትህን ለማሻሻል የሚረዱ እርምጃዎችን ውሰድ

ጤንነትህን ለማሻሻል የሚረዱ እርምጃዎችን ውሰድ

ጤንነትህን ለማሻሻል የሚረዱ እርምጃዎችን ውሰድ

በዚህ መጽሔት የመጀመሪያ ርዕስ ላይ የተጠቀሰውን ራምን ታስታውሰዋለህ? በዓለም ዙሪያ እንዳሉ ብዙ ሰዎች ሁሉ ራምም ተገቢ የሆነ አመጋገብና ሌሎች የዕለት ተዕለት ልማዶች ለጤና ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ አያውቅም ነበር። እንዲህ በማለት ይናገራል፦ “ንቁ! መጽሔት ላይ የወጣው ‘የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ይቻላል’ (ሰኔ 2002) የሚለው ርዕስ ስለተመጣጠነ ምግብ የተሻለ ግንዛቤ ሊኖረን የሚገባው ለምን እንደሆነ እንዳስተውል ረድቶኛል።”

አክሎም እንዲህ ብሏል፦ “ከመጽሔቱ የተማርነውን ነገር በቤተሰብ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት አደረግን። ከጥቂት ጊዜ በኋላ በሽታ የመከላከል አቅማችን እንደተጠናከረ ተገነዘብን። ለምንመገበው የምግብ ዓይነት ትኩረት መስጠት ከመጀመራችን በፊት ጉንፋን ያጠቃን ነበር፤ አሁን ግን እምብዛም አይዘንም። በተጨማሪም ‘ጤንነትህን ለመጠበቅ የሚረዱ ስድስት መንገዶች’ (ጥቅምት 2003) የሚል ርዕስ ይዞ ለወጣው ንቁ! መጽሔት ምስጋና ይግባውና በአነስተኛ ወጪና በቀላሉ ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ማግኘት ስለምንችልባቸው መንገዶች ተማርን።

“የቤተሰቤን ጤንነት ለማሻሻል የረዳኝ ሌላው የንቁ! መጽሔት ርዕስ ደግሞ በጥር 2004 ላይ የወጣው ‘ሳሙና “ራስህ የምትወስደው ክትባት”’ የሚለው ርዕስ ነበር። በዚህ ርዕስ ላይ የቀረቡትን ምክሮች እንዳነበብን ወዲያውኑ ተግባራዊ አደረግናቸው። አሁን እንደበፊቱ በዓይን ሕመም አንሠቃይም።

“በምንኖርበት አካባቢ ሰዎች ስለሚርመሰመሰው የዝንብና የትንኝ መንጋ ደንታ የላቸውም። የእኛ ቤተሰብ ግን መጽሐፍ ቅዱስ​—በአንተ ሕይወት ውስጥ ያለው ኃይል * (እንግሊዝኛ) ከሚለው የቪዲዮ ፊልም እንዲህ ካሉት ነፍሳት ራሳችንን መጠበቅ እንዳለብን ተምሯል። ይህ እውቀትም ቢሆን ጤንነታችንን ጠብቀን እንድንኖር ረድቶናል።”

ተስፋ አትቁረጥ! ማድረግ የሚያስፈልግህ ማስተካከያ ምንም ይሁን ምን፣ ቀስ በቀስ በመጀመርና ሊደረስባቸው የሚችሉ ግቦችን በማውጣት እያደር ስኬት ልታገኝ ትችላለህ። ለምሳሌ ያህል፣ ለጤና እምብዛም ተስማሚ ያልሆኑ ምግቦችን በአንዴ ከመተው ይልቅ እየቀነስክ ለመሄድ ጥረት አድርግ። ትንሽ ቀደም ብለህ ለመተኛትና ከወትሮው በለጥ ያለ የሰውነት እንቅስቃሴ ለማድረግ ሞክር። በትንሹም ቢሆን አንድ ነገር ማድረግ ምንም ካለማድረግ ይሻላል። እንደሚታወቀው ጥሩ የሆነ አዲስ ልማድ እስኪዳብር ድረስ ሳምንታት ወይም ወራት ሊፈጅ ይችላል። እስከዚያው ድረስ በምታደርገው ተጨማሪ ጥረት ወዲያውኑ ጥቅም ባታገኝ ተስፋ አትቁረጥ። እንቅፋቶች ቢኖሩም ጥረት ማድረግህን ከቀጠልክ ጤንነትህ መሻሻሉ አይቀርም።

በዚህ ፍጽምና በጎደለው ዓለም ውስጥ ማንም ሰው ቢሆን ፍጹም ጤንነት ሊኖረው አይችልም። ከታመምክ አንተ ጥንቃቄ ባለማድረግህ ሳይሆን በወረስከው ሰብዓዊ አለፍጽምና ምክንያት ሊሆን ይችላል። በመሆኑም ከጤና ጋር በተያያዘም ይሁን በሌላ ጉዳይ ከመጠን በላይ አትጨነቅ። ኢየሱስ “ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ርዝማኔ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ይኖራል?” በማለት ጠይቋል። (ሉቃስ 12:25) ከዚህ ይልቅ ሳያስፈልግ ዕድሜህን ሊያሳጥሩና ከሕይወት የምታገኘውን ደስታ ሊቀንሱ የሚችሉ ነገሮችን ለማስወገድ ጥረት አድርግ። እንዲህ ማድረግህ “‘ታምሜአለሁ’ የሚል” ሰው የማይኖርበት የአምላክ አዲስ ዓለም እስኪመጣ ድረስ የተሻለ ጤንነት እንድታገኝ ሊረዳህ ይችላል።​—ኢሳይያስ 33:24

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.5 በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ።