በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በይሖዋ እንደምንታመን የምናሳይባቸው ሦስት መንገዶች

በይሖዋ እንደምንታመን የምናሳይባቸው ሦስት መንገዶች

ዳዊት ጎልያድን ማሸነፍ የቻለው በይሖዋ ስለታመነ ነው። (1ሳሙ 17:45) ይሖዋ ለሁሉም አገልጋዮቹ ብርታቱን ማሳየት ይፈልጋል። (2ዜና 16:9) በራሳችን ተሞክሮና ችሎታ ሳይሆን ይሖዋ በሚሰጠው እርዳታ እንደምንታመን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? እስቲ ሦስት መንገዶችን እንመልከት፦

  • አዘውትራችሁ ጸልዩ። ስህተት ከሠራችሁ በኋላ ይቅርታ ለመጠየቅ ብቻ ሳይሆን ስህተት ለመሥራት የሚፈትን ሁኔታ ሲያጋጥማችሁ ብርታት ለማግኘትም ጸልዩ። (ማቴ 6:12, 13) ይሖዋ አስቀድማችሁ የወሰናችሁትን ነገር እንዲባርክላችሁ ከመለመን ይልቅ ውሳኔ ከማድረጋችሁ በፊት መመሪያና ጥበብ እንዲሰጣችሁ ጸልዩ።—ያዕ 1:5

  • መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብና የማጥናት ልማድ ይኑራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ አንብቡ። (መዝ 1:2) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሱ ሰዎች ታሪክ ላይ አሰላስሉ፤ እንዲሁም ያገኛችሁትን ትምህርት ተግባራዊ አድርጉ። (ያዕ 1:23-25) ከስብከቱ ሥራ ጋር በተያያዘ በራሳችሁ ተሞክሮ ከመመካት ይልቅ አገልግሎት ከመውጣታችሁ በፊት ተዘጋጁ። ለጉባኤ ስብሰባዎች አስቀድማችሁ በመዘጋጀት ከስብሰባዎቹ ሙሉ ጥቅም አግኙ

  • ከይሖዋ ድርጅት ጋር ተባብራችሁ ሥሩ። ድርጅቱ ካወጣቸው ወቅታዊ መመሪያዎች ጋር በሚገባ ተዋወቁ፤ እንዲሁም መመሪያዎቹን ዛሬ ነገ ሳትሉ ተግባራዊ አድርጉ። (ዘኁ 9:17) ሽማግሌዎች የሚሰጡትን ምክርና መመሪያ አዳምጡ።—ዕብ 13:17

ስደትን የምንፈራበት ምንም ምክንያት የለም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

• በቪዲዮው ላይ የታዩት ወንድሞችና እህቶች ምን ነገሮች አስፈርተዋቸው ነበር?

• ፍርሃታቸውን እንዲያሸንፉ የረዳቸው ምንድን ነው?