በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 04

አምላክ ማን ነው?

አምላክ ማን ነው?

የሰው ልጆች ከተፈጠሩበት ጊዜ አንስቶ ማለት ይቻላል፣ ልዩ ልዩ ወንድና ሴት አማልክትን ሲያመልኩ ቆይተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን “ከሌሎች አማልክት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ” የሆነ አንድ አምላክ እንዳለ ይናገራል። (2 ዜና መዋዕል 2:5) ይህ አምላክ ማን ነው? ሰዎች ከሚያመልኳቸው ሌሎች አማልክት ሁሉ የሚበልጠውስ በምንድን ነው? ይህ አምላክ ስለ እሱ እንድታውቅ የሚፈልጋቸው መረጃዎች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ተብራርተዋል።

1. የአምላክ ስም ማን ነው? አምላክ ስሙን እንድናውቅ እንደሚፈልግስ በምን እናውቃለን?

አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ራሱን ለእኛ አስተዋውቋል። “እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው” ብሏል። (ኢሳይያስ 42:5, 8⁠ን አንብብ።) “ይሖዋ” የሚለው ቃል ከዕብራይስጥ የተወሰደ ነው፤ ይህ ስም “እንዲሆን ያደርጋል” የሚል ትርጉም እንዳለው ይታመናል። ይሖዋ ስሙን እንድናውቅ ይፈልጋል። (ዘፀአት 3:15) ይህን በምን እናውቃለን? አምላክ ስሙ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከ7,000 ጊዜ በላይ እንዲጠቀስ አድርጓል! a ይሖዋ የሚለው ስም “በላይ በሰማይም ሆነ በታች በምድር እውነተኛው አምላክ” ብቻ ሊጠራበት የሚችል ስም ነው።—ዘዳግም 4:39

2. መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ይሖዋ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ከሚያመልኳቸው አማልክት መካከል ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ይሖዋ እንደሆነ ይናገራል። ለምን? የተለያዩ ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። ይሖዋ ከማንም የበለጠ ሥልጣን ያለው ሲሆን “በመላው ምድር ላይ ልዑል” የሆነው እሱ ብቻ ነው። (መዝሙር 83:18⁠ን አንብብ።) “ሁሉን ቻይ” ስለሆነ የፈለገውን ሁሉ ለማድረግ የሚያስችል ኃይል አለው። “ሁሉንም ነገሮች” ማለትም ጽንፈ ዓለምንም ሆነ በምድር ላይ ያለውን ሕይወት በሙሉ ‘የፈጠረው’ እሱ ነው። (ራእይ 4:8, 11) ይሖዋ ያልነበረበት ጊዜ የለም፤ ወደፊትም ለዘላለም ይኖራል። ይህም ከሌሎች የተለየ ያደርገዋል።—መዝሙር 90:2

ጠለቅ ያለ ጥናት

በአምላክ የማዕረግ ስሞችና ልዩ በሆነው ስሙ መካከል ያለውን ልዩነት እንመለከታለን። ከዚያም ስሙን ያሳወቀን ለምን እና እንዴት እንደሆነ እንማራለን።

3. አምላክ ብዙ የማዕረግ ስሞች ቢኖሩትም የግል ስሙ ግን አንድ ነው

በማዕረግ ስምና በስም መካከል ያለውን ልዩነት ለማወቅ ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • እንደ “ጌታ” ባሉት የማዕረግ ስሞችና በስም መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ብዙ አማልክትንና ጌቶችን እንደሚያመልኩ ይናገራል። መዝሙር 136:1-3ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • ‘የአማልክት አምላክ’ እና ‘የጌቶች ጌታ’ የተባለው ማን ነው?

4. ይሖዋ ስሙን እንድታውቅና እንድትጠቀምበት ይፈልጋል

ይሖዋ ስሙን እንድታውቅ እንደሚፈልግ በምን እርግጠኛ መሆን ትችላለህ? ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ስሙ እንዲታወቅ የሚፈልግ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

ይሖዋ ሰዎች ስሙን እንዲጠቀሙበት ይፈልጋል። ሮም 10:13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ የሚለውን የአምላክ ስም መጠቀም በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

  • አንድ ሰው ስምህን አስታውሶ ሲጠራህ ምን ይሰማሃል?

  • ይሖዋ በስሙ ስትጠቀም ምን የሚሰማው ይመስልሃል?

5. ይሖዋ ወደ እሱ እንድትቀርብ ይፈልጋል

ሶቴን የተባለች በካምቦዲያ የተወለደች አንዲት ሴት የአምላክን ስም ማወቅ ‘ልዩ ስሜት እንደሚፈጥር’ ተናግራለች። ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ እንደታየው ሶቴን የአምላክን ስም ማወቋ በሕይወቷ ላይ ለውጥ ያመጣው እንዴት ነው?

ከአንድ ሰው ጋር ወዳጅ ለመሆን በአብዛኛው በቅድሚያ ስሙን ማወቅ ያስፈልግሃል። ያዕቆብ 4:8ሀን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ይሖዋ ምን ግብዣ አቅርቦልሃል?

  • የአምላክን ስም ማወቅህና በስሙ መጠቀምህ ወደ እሱ ለመቅረብ የሚረዳህ እንዴት ነው?

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “አምላክ እንደሆነ አንድ ነው፤ በፈለግከው ስም ብትጠራው ለውጥ የለውም።”

  • የአምላክ ስም ይሖዋ እንደሆነ ታምናለህ?

  • አምላክ በስሙ እንድንጠቀም እንደሚፈልግ ለሌሎች ማስረዳት የምትችለው እንዴት ነው?

ማጠቃለያ

ብቸኛው እውነተኛው አምላክ ስሙ ይሖዋ ነው። ይሖዋ ወደ እሱ እንድንቀርብ ስለሚፈልግ ስሙን እንድናውቀውና እንድንጠቀምበት ያበረታታናል።

ክለሳ

  • ይሖዋ ሰዎች ከሚያመልኳቸው ሌሎች አማልክት ሁሉ የሚለየው እንዴት ነው?

  • የአምላክን ስም መጠቀም ያለብን ለምንድን ነው?

  • ይሖዋ ወደ እሱ እንድትቀርብ እንደሚፈልግ በምን ማወቅ ትችላለህ?

ግብ

ምርምር አድርግ

በአምላክ መኖር እንድናምን የሚያደርጉ አምስት አሳማኝ ማስረጃዎችን ተመልከት።

“አምላክ አለ?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

‘አምላክ ምንጊዜም ነበረ’ ብሎ ማመን ምክንያታዊ የሆነው ለምን እንደሆነ አንብብ።

“አምላክን ማን ፈጠረው?” (መጠበቂያ ግንብ ነሐሴ 1, 2014)

የአምላክ ስም በጥንት ዘመን እንዴት ይጠራ እንደነበር ባናውቅም ስሙን መጠቀም ያለብን ለምን እንደሆነ አንብብ።

“ይሖዋ ማን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

አምላክን ለመጥራት የምንጠቀምበት ስም ለውጥ ያመጣል? የአምላክ የግል ስም አንድ ብቻ ነው የምንልበትን ምክንያት ተመልከት።

“አምላክ ስንት ስሞች አሉት?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

a የአምላክን ስም ትርጉምና አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን ስም ያልተጠቀሙበትን ምክንያት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጨማሪ መረጃ ሀ4⁠ን ተመልከት።