መዝሙር 46:1-11

  • ‘አምላክ መጠጊያችን ነው’

    • የአምላክ አስደናቂ ሥራዎች (8)

    • አምላክ ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል (9)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የቆሬ ልጆች መዝሙር።+ በአላሞት ቅኝት።* 46  አምላክ መጠጊያችንና ብርታታችን፣+በጭንቅ ጊዜ ፈጥኖ የሚደርስልን ረዳታችን ነው።+   በመሆኑም በምድር ላይ ነውጥ ቢከሰት፣ተራሮች ተንደው ወደ ጥልቁ ባሕር ቢሰምጡ አንፈራም፤+   ውኃዎቹ ቢያስገመግሙና አረፋ ቢደፍቁ፣+ተራሮችም ከውኃዎቹ ነውጥ የተነሳ ቢንቀጠቀጡ አንሸበርም። (ሴላ)   የአምላክን ከተማ+ ደስ የሚያሰኙ ጅረቶች ያሉት ወንዝ አለ፤ከተማዋም የልዑሉ አምላክ የተቀደሰ ታላቅ ማደሪያ ነች።   አምላክ በከተማዋ ውስጥ ነው፤+ እሷም አትንኮታኮትም። ጎህ ሲቀድ አምላክ ይደርስላታል።+   ብሔራት ሁከት ፈጠሩ፤ መንግሥታት ተገለበጡ፤እሱ ድምፁን ከፍ አድርጎ አሰማ፤ ምድርም ቀለጠች።+   የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው፤+የያዕቆብ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያችን ነው። (ሴላ)   ኑና የይሖዋን ሥራዎች እዩ፤በምድርም ላይ አስደናቂ ነገሮችን እንዴት እንዳከናወነ ተመልከቱ።   ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።+ ቀስትን ይሰባብራል፤ ጦርንም ያነክታል፤የጦር ሠረገሎችን* በእሳት ያቃጥላል። 10  “አርፋችሁ ተቀመጡ፤ እኔ አምላክ እንደሆንኩም እወቁ። በብሔራት መካከል ከፍ ከፍ እላለሁ፤+በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”+ 11  የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ከእኛ ጋር ነው፤+የያዕቆብ አምላክ አስተማማኝ መጠጊያችን ነው።+ (ሴላ)

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ጋሻዎችን” ማለትም ሊሆን ይችላል።