መዝሙር 73:1-28

  • ፈሪሃ አምላክ ያለው ሰው መንፈሳዊነቱን መልሶ አጠናከረ

    • “እግሮቼ ከመንገድ ሊወጡ ተቃርበው ነበር” (2)

    • ‘ቀኑን ሙሉ ተጨነቅኩ’ (14)

    • ‘ወደ አምላክ መቅደስ እስክገባ ድረስ’ (17)

    • ክፉዎች በሚያዳልጥ መሬት ላይ ናቸው (18)

    • “ወደ አምላክ መቅረብ ይበጀኛል” (28)

የአሳፍ+ ማህሌት። 73  አምላክ ለእስራኤል፣ ልባቸው ንጹሕ ለሆነ ሁሉ በእርግጥ ጥሩ ነው።+   እኔ ግን እግሮቼ ከመንገድ ሊወጡ ተቃርበው ነበር፤አዳልጦኝ ልወድቅ ምንም አልቀረኝም።+   ክፉ ሰዎች ያላቸውን ሰላም በተመለከትኩ ጊዜ፣እብሪተኛ በሆኑ ሰዎች* ቀንቼ ነበርና።+   ሳይሠቃዩ ይሞታሉና፤ሰውነታቸው ጤናማ* ነው።+   እንደ ሌሎች ሰዎች ችግር አያጋጥማቸውም፤+እንደ ሌሎች ሰዎችም መከራ አይደርስባቸውም።+   ስለዚህ ትዕቢት የአንገት ጌጣቸው ነው፤+ዓመፅም እንደ ልብስ ይሸፍናቸዋል።   ከብልጽግናቸው* የተነሳ ዓይናቸው ፈጧል፤ልባቸው ካሰበው በላይ አግኝተዋል።   በሌሎች ላይ ያፌዛሉ፤ ክፉ ነገርም ይናገራሉ፤+ ሌሎችን ለመጨቆን በእብሪት ይዝታሉ።+   የሰማይን ያህል ከፍ ያሉ ይመስል በእብሪት ይናገራሉ፤በአንደበታቸው እንዳሻቸው እየተናገሩ በምድር ላይ ይንጎራደዳሉ። 10  በመሆኑም ሕዝቡ ወደ እነሱ ይሄዳል፤ከእነሱ የተትረፈረፈ ውኃም ይጠጣል። 11  እነሱም “አምላክ እንዴት ያውቃል?+ ልዑሉ አምላክ በእርግጥ እውቀት አለው?” ይላሉ። 12  አዎ፣ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ሁልጊዜ ሳይጨናነቁ ይኖራሉ።+ የሀብታቸውንም መጠን ያሳድጋሉ።+ 13  በእርግጥም ልቤን ያነጻሁት፣ንጹሕ መሆኔንም ለማሳየት እጄን የታጠብኩት በከንቱ ነው።+ 14  ቀኑን ሙሉም ተጨነቅኩ፤+በየማለዳውም ተቀጣሁ።+ 15  እነዚህን ነገሮች ተናግሬ ቢሆን ኖሮ፣ሕዝብህን* መክዳት ይሆንብኝ ነበር። 16  ይህን ለመረዳት በሞከርኩ ጊዜ፣የሚያስጨንቅ ሆነብኝ፤ 17  ይኸውም ወደ ታላቁ የአምላክ መቅደስ እስክገባናየወደፊት ዕጣቸውን እስክረዳ ድረስ ነበር። 18  በእርግጥም በሚያዳልጥ መሬት ላይ ታስቀምጣቸዋለህ።+ ለጥፋት እንዲዳረጉም ትጥላቸዋለህ።+ 19  እንዴት በቅጽበት ጠፉ!+ በአስደንጋጭ ሁኔታ ተደመሰሱ! የደረሰባቸው ጥፋት ቅጽበታዊ ነው! 20  ይሖዋ ሆይ፣ ሰው ከእንቅልፉ ሲነሳ እንደሚረሳው ሕልም፣አንተም በምትነሳበት ጊዜ ምስላቸውን ታስወግዳለህ።* 21  ሆኖም ልቤ ተመሯል፤+ውስጤንም* ውጋት ቀስፎ ይዞታል። 22  እኔም ማመዛዘን የማልችልና ማስተዋል የጎደለኝ ሆኜ ነበር፤በአንተ ፊት ማሰብ እንደማይችል እንስሳ ሆንኩ። 23  አሁን ግን ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነኝ፤አንተም ቀኝ እጄን ይዘሃል።+ 24  በምክርህ ትመራኛለህ፤+በኋላም ክብር ታጎናጽፈኛለህ።+ 25  በሰማይ ማን አለኝ? በምድርም ላይ ከአንተ ሌላ የምሻው የለም።+ 26  ሰውነቴም ሆነ ልቤ ሊዝል ይችላል፤አምላክ ግን ለዘላለም የልቤ ዓለትና ድርሻዬ ነው።+ 27  ከአንተ የሚርቁ በእርግጥ ይጠፋሉ። አንተን በመተው ብልሹ ምግባር የሚፈጽሙትን* ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ።*+ 28  እኔ ግን ወደ አምላክ መቅረብ ይበጀኛል።+ ሥራዎቹን ሁሉ እንዳውጅ+ሉዓላዊውን ጌታ ይሖዋን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጉራቸውን በሚነዙ ሰዎች።”
ወይም “ቦርጫቸው የሰባ።”
ቃል በቃል “ከስባቸው።”
ቃል በቃል “የወንዶች ልጆችህን ትውልድ።”
ቃል በቃል “ምስላቸውን ትንቃለህ።”
ቃል በቃል “ኩላሊቴንም።”
ወይም “ታማኞች ሳይሆኑ የሚቀሩትን።”
ቃል በቃል “ዝም ታሰኛቸዋለህ።”