በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደስታ የሚያስገኝ መንገድ

መንገዱን ማግኘት

መንገዱን ማግኘት

ደስተኛ እንደሆንክ ይሰማሃል? ከሆነ ደስተኛ ያደረገህ ምንድን ነው? ቤተሰብህ፣ ሥራህ ወይም ሃይማኖትህ ነው? አሊያም ደግሞ ደስተኛ ሊያደርግህ የሚችልን ነገር በተስፋ እየተጠባበቅክ ይሆናል፤ ለምሳሌ ትምህርትህን የምትጨርስበትን፣ ጥሩ ሥራ የምትይዝበትን አሊያም አዲስ መኪና የምትገዛበትን ጊዜ በጉጉት እየጠበቅክ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ሰዎች አንድ ግብ ላይ ሲደርሱ ወይም የፈለጉትን ነገር ሲያገኙ ደስታ ይሰማቸዋል። ይሁን እንጂ እንዲህ ያለው ደስታ ለምን ያህል ጊዜ ይዘልቃል? በአብዛኛው ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ አይደለም፤ ይህ ደግሞ ለሐዘን የሚዳርግ ነው።

ደስታ ‘አንጻራዊ ዘለቄታ ያለው የደህንነት ስሜት’ የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። በተጨማሪም ከእርካታ አንስቶ ጥልቅና ከፍተኛ እስከሆነ ውስጣዊ ፍስሐ ድረስ ባሉት ስሜቶች እንዲሁም እነዚህ ስሜቶች እንዲቀጥሉ ባለን ተፈጥሯዊ ፍላጎት ይንጸባረቃል።

ደስታ ዘላቂ የሆነ የደህንነት ስሜት ከመሆኑ አንጻር የተወሰነ መንገድ ተጉዘን እንደምንደርስበት ቦታ ወይም ግብ ሳይሆን እንደ ረጅም ጉዞ ተደርጎ ተገልጿል። “ይህን ሳገኝ ወይም እዚህ ላይ ስደርስ ደስተኛ እሆናለሁ” የሚል ሰው ደስተኛ የሚሆንበትን ጊዜ እያራዘመ ነው ሊባል ይችላል።

ደስታን ከጥሩ ጤንነት ጋር ልናመሳስለው እንችላለን። ጥሩ ጤንነት ሊኖረን የሚችለው እንዴት ነው? ጤናማ የአመጋገብ ልማድ ማዳበርንና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግን ጨምሮ በመላው ሕይወታችን ጥበብ የሚንጸባረቅበት ጎዳና በመከተል ነው። ከደስታ ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ደስታ የሚገኘው በሕይወት ውስጥ ጥሩ ጎዳናን በመከተልና አስተማማኝ ከሆኑ መመሪያዎች ጋር ተስማምቶ በመኖር ነው።

ታዲያ ደስታ በሚያስገኘው መንገድ ላይ እንድንጓዝ የሚያስችሉን ባሕርያት ወይም የአኗኗር ዘይቤዎች የትኞቹ ናቸው? አንዳንዶቹ ከሌሎቹ ይበልጥ አስፈላጊ ቢሆኑም ቀጥሎ የተገለጹት ነጥቦች በሙሉ በዚህ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ፦

  • ባለን መርካትና ለጋስ መሆን

  • ጥሩ ጤንነትና ችግርን ተቋቁሞ የመኖር ችሎታ

  • ፍቅር

  • ይቅር ባይነት

  • ዓላማ ያለው ሕይወት

  • ተስፋ

ጥበብ ያዘሉ ምክሮችን የያዘ አንድ ትልቅ ግምት የሚሰጠው መጽሐፍ “በመንገዳቸው ነቀፋ የሌለባቸው . . . ደስተኞች ናቸው” ይላል። (መዝሙር 119:1) እስቲ እዚህ ላይ ስለተጠቀሰው መንገድ ይበልጥ እንመርምር።