በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

አምላክ፣ እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበሩበት ጊዜ እነሱን ለመመገብ ድርጭቶችን የመረጠው ለምን ነበር?

እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡ በኋላ አምላክ እነሱን ሥጋ ለመመገብ በሁለት የተለያዩ አጋጣሚዎች በርካታ ድርጭቶችን ሰጥቷቸዋል።​—ዘፀአት 16:13፤ ዘኍልቍ 11:31

ድርጭቶች 18 ሴንቲ ሜትር ገደማ ርዝመትና 100 ግራም ያህል ክብደት ያላቸው ትናንሽ ወፎች ናቸው። እነዚህ ወፎች የመራቢያ ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት በምዕራብ እስያና በአውሮፓ በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ነው። ድርጭቶች የክረምቱን ወቅት ለማሳለፍ ወደ ሰሜን አፍሪካና ወደ ዓረብ አገራት ይፈልሳሉ። የሚፈልሱበት ወቅት ሲደርስ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ድርጭቶች የሜድትራንያንን ባሕር ምሥራቃዊ ዳርቻ አቋርጠው በሲና ባሕረ ገብ መሬት ላይ ይበራሉ።

ዘ ኒው ዌስትሚንስትር ዲክሽነሪ ኦቭ ዘ ባይብል እንደገለጸው ከሆነ ድርጭቶች “በፍጥነትና ቅልጥፍና ባለው መንገድ የሚበርሩ ከመሆኑም ሌላ ነፋሱ የሚነፍስበትን አቅጣጫ ተከትለው የሚጓዙ ወፎች ናቸው፤ ሆኖም ነፋሱ አቅጣጫ ከቀየረ ወይም ወፎቹ ለረጅም ሰዓት ከመብረራቸው የተነሳ ከዛሉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ድርጭቶች መሬት ላይ ይወድቃሉ፤ መንቀሳቀስ አቅቷቸውም ባሉበት ይቆያሉ።” ጉዟቸውን ከመቀጠላቸው በፊት ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን መሬት ላይ መቆየት ይኖርባቸዋል፤ ይህ ደግሞ የአዳኞች ሲሳይ ያደርጋቸዋል። በ20ኛው መቶ ዘመን መጀመሪያ ላይ ግብፅ ለምግብነት የሚሆኑ ሦስት ሚሊዮን ድርጭቶችን በየዓመቱ ለውጭ ገበያ ታቀርብ ነበር።

እስራኤላውያን ድርጭቶች የተመገቡባቸውን ሁለቱንም አጋጣሚዎች ከተመለከትን ጊዜው የጸደይ ወቅት እንደነበር እንረዳለን። ምንም እንኳ ድርጭቶች በዚህ ወቅት ላይ በሲና አካባቢ አዘውትረው የሚበርሩ ቢሆንም እነዚህ ወፎች እስራኤላውያን በሰፈሩባቸው አካባቢዎች እንዲወድቁ ለማድረግ ‘ነፋስ ያመጣው’ ይሖዋ ነው።​—ዘኍልቍ 11:31

በዮሐንስ 10:22 ላይ የተጠቀሰው “የመታደስ በዓል” ምንድን ነው?

አምላክ፣ አይሁዳውያን እንዲያከብሩ ያዘዘው ሦስት በዓላትን ሲሆን እነዚህም በጸደይ ወቅት መባቻ የሚከበረው ያልቦካ ቂጣ በዓል፣ በጸደይ ወቅት መገባደጃ የሚከበረው የጴንጤቆስጤ በዓል እንዲሁም በመጸው ወቅት የሚከበረው የመክተቻ በዓል ናቸው። ይሁንና በዮሐንስ 10:22 ላይ የተጠቀሰው በዓል የሚከበረው “ክረምት” ላይ ነው፤ ይህ በዓል የይሖዋ ቤተ መቅደስ በ165 ዓ.ዓ. በድጋሚ የተወሰነበትን ጊዜ ለማሰብ የሚከበር ነው። በዓሉ ቀኖቹ አጭር የሚሆኑበት ወቅት ከሚቃረብበት ካሴሉ ወይም ኪስሌው ከተባለው ወር 25ኛ ቀን አንስቶ ለስምንት ቀናት ይከበራል። ይህ በዓል እንዲከበር ምክንያት የሆነው ነገር ምንድን ነው?

በ168 ዓ.ዓ. የሶርያው ሰሉሲዳዊ ገዥ አንታይከስ አራተኛ (ኤፒፋነስ) የአይሁዳውያንን እምነትና ልማድ ለማጥፋት ጥረት ያደረገ ሲሆን በኢየሩሳሌም በይሖዋ ቤተ መቅደስ ውስጥ በሚገኘው መሠዊያ ላይ ለአረማዊ አማልክት መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ አቁሞ ነበር። በዚህ መሠዊያ ላይ የግሪክ አምላክ ለሆነው ለዙስ መሥዋዕቶችን ያቀርብ ነበር።

ይህ ድርጊት መቃባውያን ለዓመፅ እንዲነሳሱ አድርጓቸዋል። የአይሁዳውያን መሪ የነበረው ይሁዳ መቃቢስ ኢየሩሳሌምን ከሰሉሲዳውያን ላይ አስመለሰ፤ እንዲሁም ረክሶ የነበረውን መሠዊያ አፍርሶ በዚያ ቦታ ላይ አዲስ መሠዊያ ሠራ። የቀድሞው መሠዊያ ከረከሰ ከሦስት ዓመት በኋላ ይሁዳ ከአረማውያን አምልኮ ሙሉ በሙሉ የጸዳውን ቤተ መቅደስ ለይሖዋ በድጋሚ ወሰነ። አይሁዳውያን ከዚያን ጊዜ አንስቶ በታኅሣሥ ወር ላይ ይህን “የመታደስ በዓል” (በዕብራይስጥ ኻኑካ) ያከብራሉ። በዛሬው ጊዜ ይህ በዓል ሃኑካ ተብሎ ይጠራል።

[በገጽ 14 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የይሁዳ መቃቢስ ምስል ሊዮን፣ 1553

[በገጽ 14 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

From the book Wood’s Bible Animals. 1876