በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትምህርት 1

ምሥራቹ ምንድን ነው?

ምሥራቹ ምንድን ነው?

1. ከአምላክ የመጣው ምሥራች ምንድን ነው?

አምላክ፣ ሰዎች በምድር ላይ ተደስተው እንዲኖሩ ይፈልጋል። ምድርንና በውስጧ ያሉትን ነገሮች በሙሉ የፈጠረው የሰው ልጆችን ስለሚወድ ነው። አምላክ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ አስደሳች ሕይወት እንዲያገኙ የሚያደርግ እርምጃ በቅርቡ ይወስዳል። ለሰው ልጆች ሥቃይ ምክንያት የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ያስወግዳል።​—ኤርምያስ 29:11ን አንብብ።

እስካሁን ዓመፅን፣ በሽታን ወይም ሞትን ማስወገድ የቻለ አንድም መንግሥት የለም። ሆኖም አምላክ የምሥራች ልኮልናል፤ በቅርቡ ሁሉንም ሰብዓዊ መንግሥታት አስወግዶ የእሱ መንግሥት ምድርን እንዲገዛ ያደርጋል። የዚህ መንግሥት ተገዢዎች ሰላምና የተሟላ ጤንነት ይኖራቸዋል።​—ኢሳይያስ 25:8ን፣ 33:24ን እና ዳንኤል 2:44ን አንብብ።

2. ምሥራቹ በዛሬው ጊዜ በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

መከራና ሥቃይ ሊወገድ የሚችለው አምላክ መጥፎ ሰዎችን ሲያጠፋ ብቻ ነው። (ሶፎንያስ 2:3) ይሁንና ይህ የሚሆነው መቼ ነው? የአምላክ ቃል፣ የሰው ዘር የገጠሙት አሳሳቢ ሁኔታዎች በዘመናችን እንደሚኖሩ አስቀድሞ ተናግሮ ነበር። በአሁኑ ጊዜ ያሉት ሁኔታዎች፣ አምላክ እርምጃ የሚወስድበት ጊዜ ቅርብ እንደሆነ ይጠቁማሉ።​—2 ጢሞቴዎስ 3:1-5ን አንብብ።

3. ምን ማድረግ ይኖርብናል?

የአምላክ ቃል ከሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ መማር ይኖርብናል። ይህ መጽሐፍ ከአፍቃሪ አባታችን እንደተላከልን ደብዳቤ ነው። በዛሬው ጊዜ የተሻለ ሕይወት መምራት የምንችልበትን መንገድ የሚነግረን ከመሆኑም ሌላ ወደፊት በምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ይጠቁመናል። እርግጥ አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ከሌሎች ጋር መወያየትህ ላያስደስታቸው ይችላል። ያም ሆኖ የሌሎች አመለካከት፣ አምላክ ቃል የገባው የዘላለም ሕይወት ተስፋ እንዲያመልጥህ ሊያደርግ አይገባም።​—ምሳሌ 29:25ን እና ራእይ 14:6, 7ን አንብብ።